Jump menu contains no items!

Amharic

Attention Skyline Residents: Important Health Information

ማሳሰቢያ:  በ SHARE ፕሮግራም በደማቸው ውሰጥ ስኳር ላልባቸው ነዋሪዎች

በሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ ሼር ፕሮግራም በኩል ስካይላይን ታወርስ ውስጥ ከዲሴምቤር 2010 እስከ ኤፕሪል 2014 የደም ምርመራ ካደረጉ፤ ለተወሰኑ በቫይረስ ለሚተላለፉ በሽታዎች ምርመራ ሊያደርጉ ይገባል። በሼር ፕሮግራም ውስጥ ካልተሳተፉ ይህ መልእክት አይመለከትዎትም።

 

እስከ አሁን ድረስ በደም ምርመራው ምክንያት የተላላፊ በሽታ ተጠቂ የሆነ ሰው የለም። መርፌዎቹ ከአንድ ግዜ በላይ ጥቅም ላይ አልዋሉም፤ ነገር ግን መርፌዎቹን የሚይዘው መሳሪያ የሄፐታይተስ ቢ የማስተላለፍ አቅም እንዳለው ታውቋል። የመተላለፍ እድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም፤ ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። የዘወትር ሃኪሞ ጋር በመሄድም ይህንን ምርመራ እንዲደረግልዎ መጠየቅ ይችላሉ። 

 

ቤተሰብዎን ከኩፍኝ በሽታ ይከላከሉ

ኩፍኝ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በእስያ በሚኖሩ በርካታ አገሮች ውስጥ     በስፋት የሚገኝ አደገኛ በሽታ ነው።

አስቀድመው ክትባቱን ካልወሰዱ ወይም ኩፍኝ ወጥቶላቸው ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም የቤተሰብ አባል ከጉዞ በፊት የኩፍኝ ክትባት    መውሰድ ይኖርበታል።